ሜጀር ጄኔራል ፋንታ በላይ ከፊታውራሪ በላይ ውንዱ እማሆይ ናፈቁ በለው ከአገሪቱ ባለውለታ አርበኞች አብራክ በጎንደር ክፍለ ሀገር በሊቦ አውራጃ በበለሳ ወረዳ በ1929 ዓ.ም. ተወለዱ።
በ1939 ዓ.ም. ከአርበኞች ልጆች ጋር ወደ አዲስ አበባ ተልዕከው በመድኃኒዓለም ትምህርት ቤት እንዲማሩ ተደረገ። ፋንታ በላይ ከፍተኛ ትምህርት የመቅበል ችሎታ ስለነበራቸው ከአንደኛ እስከ አስራ አንደኛ ክፍል በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከክፍላቸው ዘወትር አንደኛ በመሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀቁ። ምርጫቸውን አየር ኃይል አድርገው በ1945 ዓ.ም. በ17 ዓመት ዕድሚያቸው አየር ተቀጠሩ። በሠራዊቱ ጎበዝ ተማሪነታቸውን ቤቱ የሚሰጠውን ከፍተኛ ሽልማት አግኝተዋል። በተጨማሪም ለላቀ የትምህርትና የሙያ ውጤት ይሰጥ የነበረውን የፊሪ ትሮፊ ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተሸልመዋል።
ፋንታ በላይ በሻለቃ ማዕረግ እንዳሉ ወደ አሜሪካ ለትምህርት ዝልቀው በሴንትሉዊስ ዩኒቨርሲቲ ዓመት ጊዜ አግኝተዋል፤ የመጀመሪያውን በሴንትሉዊስ ዩኒቨርሲቲ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ውጤትና በክብር ኣንደኛና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝትዋል። የመጀመሪያውን በእድሚኒስትሬሽን ሲሆን ሁለተኛ ማለትም ማስትሬታቸውን ያገኙት በማኔጅሜንት ሳይንስ ነው። ፋንታ በላይ ሁለ ገብ ችሎታ ያላቸው በመሆኑ በስፖርተኛነትም በአንደኛ ምድብ ለአየር ኃይል በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ ወዘተ.. ለረጅም ዓመታት በመጫወት ዝናን አትርፈዋል። በርካታ ዋንጫዎችንና ድሎችን ለሠራዊቱ አስገኝተዋል።
ሜጄር ጄኔራል ፋንታ በላይ በ34 ዓመት የአየር ኃይል አገልግሎት ቆይታቸው በርካታ አኩሪ ግዳጆችን ተወጥተዋል። በበራሪነት፣ በተዋጊነት፣ በበረራ አስተማሪነት ረጅም ፍሬያማ አገልግሎት ሰጥተዋል። ፋንታ በላይ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ተልዕኮ ሀገራቸውን ወክለው በኰንጐ፣ እንዲሁም በሱማሌ የጐርፍ ማጥለቅለቅ በደረሰበት ወቅት አውሮፕላን በማብረር፣ የልብስ፣ የመድኃኒት ዕርዳታን ለተረጂዎች በማድረስ በጐ ግልጋሎት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዕድገትና መዳበር ሲነሳ እንደ ፋንታ በላይ የመሳሰሉ ታታሪ ቆራጥ የሠራዊቱ ፍሬዎች ከኃይሉ ጋር እንደ ድርና ማግ የተሣሠሩ እካል ተቆጥረው ዘወትር ይታወሳሉ። ፋንታ በላይ የኣየር ኃይሉን ዘመናዊ አሠራር በማዳበር በርካታ ድርሻዎች እበርክተዋል።
በ1967 ዓም የኢትዮጵያ ዳር ድንበር መጣስ በተፋፋመበት፣ የአገር ወገን ነፃነት መደፈር በተከሰተበት፣ በተላይም የአሥመራ ከሰባ በኣየለበት ወቅት ፋንታ በላይ የ2ኛው አየር ምድብ አዛዥ በመሆን ጀግንነት በተሞላበት ከፍተኛ ተከላካይነት፣ የአጥቂነት ተጋድሎ በማስፈጸምና በመፈጸም ጠላትን በማባረር _ የህገሪቱን ህልውና በማስከበር ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።
እንዲሁም በ1969 ዓም በምሥራቅ ጦርነት የሱማሌ ጦር የኢትዮጵያን ወሰን ጥሶ፣ በታንክ የወገንን ደጀን ሰብሮ ከዕዝ መስክ ቁንጮ መነነ፡ል ዘልቆና ከሶ አወሮፕላኖች እያቃጠለ በገፋበት ቀውጥና አጣዳሪ ወቅት ፋንታ በላይ በከፍተኛ ቆራጥነት ድፍረት በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖች በጠላት እጅ እንዳይወድቁ ወደ ሐረር ሜዳ በማሸሽ ጠቃሚና ወሳኝ እርምጃ ማድረጋቸው ለኋላው የሱማሌ ጦርነት ሽንፈት የእውሮፕላኖች መትረፍ መልሶ ጠላትን ለማጥቃት ኣስችሎ ዓይነተኛ ድልን እንዲያጐናጽፍ እድርገዋል። .
ፋንታ በላይ መረበሽና ተስፋ መቁረጥ የማይታይባቸው ዕውቅ የጦር መሪ፣ በዘመቻ እቅድ አመንጪነት፣ አመራር ሰጭነት በመካፈል ጠላትን መቆሚያ በማሳጣት፤ የሠራዊት የውጊያና ሞራል በማሳደግ የጠላትን ቅስም ሰብሮ ሰማሽነፍ፣ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ፋንታ በላይ ምሥራቅ ጦርነት እንዳሉ የአየር ኃይል አዛዥ በመሆን ለአሥር ዓመት አገልግለዋል።
ፋንታ በላይ ለአየር ኃይሉ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ አዛኝ መሆናቸውም ቢታወቅም ዳሩ ግን ባህሪናችሎታቸው ለመንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገዛዝና አሠራር ምቹ ሆነው ባለመገኘታቸው የዓይን ቁራኛ ነበረባቸው። በተለይም በሠራዊቱ ያላቸውን ተቀባይነት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በመፍራት ጭምር ከሠራዊቱ አዛኝነት በማንሳት ወደ እንዲስቱሪ ምኒስቴር እንዲዛውሩ ማድርጉ ሁሉ በዚህ ምክንያት እንደነበር ይታወቃል።
ፋንታ በላይ የኢትዮጵያን ህመም ቀደም ብለው የተረዱ ናቸው። ማብቂያና መላ ሳልተበጀለት ሂደት በተጫረው የእርስ በርስ ዕልቂት እንደ ጐርፍ የሚፈሰውን የወንድማማችነት ደም ያዩ፣ በሠራዊቱ ውስጥ ያለውን በጦርነት የመስልቸት ሁኔታ ሁሉ ያወቁና፣ ከሁሉም በላይ ሀገሪቱ ከዕለት ወደ ዕለት ወደባሰ ችግር እየዘፈቀች፣ ወገን እየተጐዳ፣ ፍትህ እየተዛባ፣ መሪና መሪዎች ያልተገናኙ መሆናቸውን የተረዱ ናቸው። ፋንታ በላይ ሀገራቸውን እጥብቀው ይወዱ ስለነበረ ጭንቀታቸውና ጥበታቸው እናት ሀገራቸው ከወደቀችበት ተነስታ፣ ሠላም ሠፍኖ የህዝብ ኑሮ ተሻሽሎ አገራቸው ወደፊት የምትገፋሰትን ሂጀት መሻት ነበር ማለት ይቻላል። ለዚህም ዓላማ መሳካት በመነሳት የግንቦት 8 1981 ዓም ወታደራዊ አመጽ በማድረግ ራሳቸውን ለመስዋዕት አቀረቡ። በግምት፡ እስከ ግንቦት 30 በእስር ላይ ቆይተው ተገድለዋል።
ፋንታ በላይ ለዓላማቸው በግንባር መፋለምን ምርጫቸው፣ ለሀገራቸውና ለወገን መሞትን ክቡር ያደረጉ ጀግና ናቸው።
ፋንታ በላይ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ድንቅነሽ ዮሐንስ በህግ ተጋብተውኑ ሁለት ልጆች እፈርተዋል።